20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በሶማሊ ክልል ደረጃ "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድት" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የባህል አውደ ርዕይን ጨምሮ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ የተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ኢብራሂም ሀሰን፥ የብሔር፣ ብሔረሰቦች በዓልን ሲከበር የህብረተሰቡን የሰላምና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራትን በማጠናከር መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል።
የበዓሉ መከበር ለዘመናት የዘለቀውን የሕዝቦች ወንድማማችነት እና አብሮነት ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ አለው ሲሉ ምክትል አፈ ጉባዔ ኢብራሂም ገልጸዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በጋራ ርብርብ በተጠናቀቀበት ማግስት የሚከበር መሆኑ የዘንድሮውን በዓል ልዩ ያደርገዋል ያሉት ምክትል አፈ ጉባዔው፤ በዓሉ የተጀመሩ በርካታ ሀገራዊ ውጥኖችን ከዳር ለማድረስ ቃላችንን የምናድስበት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
እንደ ሕዳሴ ግድብ ሁሉ ሀገራዊ ምክክሩን በስኬት በማጠናቀቅ ኢትዮጵያን በሁሉም መስኮች ምሳሌ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ebcdotstream #ethiopia #somali #jigjiga #nationalitiesday