Search

ቻይና ይፋ ያደረገችው ልዩ የኤሌክትሪክ ከባድ መኪና ምንድን ነው?

ረቡዕ ኅዳር 10, 2018 253

ቻይና በሀገሪቱ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ያለውን የአረንጓዴ ለውጥ ለማፋጠን ታስቦ የተሠራ አዲስ የኤሌክትሪክ ስማርት ከባድ መኪና (braided heavy truck) ይፋ አድርጋለች።

ይህ መኪና ከተለመዱት የኤሌክትሪክ ከባድ መኪናዎች በተለየ፣ ከላይ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች (catenary braids) ኃይልን የሚስብ በመሆኑ ረጅም ርቀት የመጓዝ አቅም ይኖረዋል ተብሏል።

መኪናው በሰው ሰራሽ አዕምሯዊ አቅም የማሽከርከር ሥርዓት (Intelligent driving system) ያለው ሲሆን፣ በንፋስና በፀሐይ ኃይል የበለጸጉ የማዕድን ማውጫ አካባቢዎችን ጨምሮ በከባድ የጭነት ማጓጓዣ ሥራዎች ላይ ያተኩራል።

ይህ አዲሱ መኪና ወደ 10 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የሙከራ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ረጅም ጉዞ በማድረግ ከባድ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ ተስፋ ተጥሎበታል።

ይህ ፕሮጀክት በቻይና የከባድ ትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ ለአካባቢ ተስማሚ እና የሰው ሰራሽ አዕምሯዊ አቅም የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ ስለመሆኑም ሽንዋ ዘግቧል።

በሰለሞን ገዳ

#ebcdotstream #china #electrictruck