የኢትዮጵያ በዱር በገደሉ ጸንቶ በመሥዋዕትነት የሀገራችንን ሰላም እና ደኅንነት እያረጋገጠ ይገኛል። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባላትም በለውጡ ዓመታት ባከናወኗቸው የሪፎርም ሥራዎች ከሰው ኃይል እስከ መሠረተ ልማት ግንባታ ያስመዘገቧቸው ለውጦች በርካታ ናቸው።
ኢትዮጵያውያን እንደ ዐይናቸው ብሌን በሚሳሱለት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የማሪን ኮማንዶ አባላት እና ባሕረኞች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በባሕር፣ በየብስ እና በምድር እየተወጡ ነው።
የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የባሕር ላይ ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያስችላቸውን የአካል እና የሥነ ልቦና ጥንካሬ ተላብሰው፣ በየዕለቱ የሚወጧቸውን ግዳጆች በስኬት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን የአካል ብቃት እያዳበሩ የባሕር ደኅንነት ሥራዎችን በመሥራት ውጤቶችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ።
አባላቱ እጅግ አስቸጋሪ በሆነው የአየር ፀባይ ውስጥ የሚያደርጓቸው የዝግጁነት ሥራዎች በሕዳሴው ዙሪያ ያለውን ተልዕኮ የሚያቀላጥፉ እና የማድረግ አቅምን የሚያረጋግጡ ተግባራት ሲሆኑ፣ የልማት ሥራዎችም መተግበራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: