Search

ፀጋዎችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን ጥረት

ረቡዕ ኅዳር 10, 2018 86

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የለማ ሰብልን በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን በክልሉ የተለያዩ የምርታማነት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።
ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ ረጂነት ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሐመድ አብዱልዓዚዝ በበኩላቸው፤ ክልሉ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ለሚጎዱ ዜጎች በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ 270 ሔክታር ማሳ ማልማቱን ገልፀዋል።
በቀጣይ ሰፋፊ የግብርና ልማቶችን በማከናወን ተደማሪ አቅም ለመፍጠር እንደሚሠራም ጠቁመዋል።
በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የማሽላ፣ የበቆሎ፣ የአኩሪ አተር እና የተለያዩ ሰብሎች እየለሙ ይገኛል።
 
በነስረዲን ሀሚድ