Search

ሕፃናት እና የመጫወት መብታቸው

ሓሙስ ኅዳር 11, 2018 114

የዘንድሮው የዓለም ሕፃናት ቀን "የሕፃናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም ሕፃናት" በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል።
በየዓመቱ ኅዳር 11 የሚከበረው የዓለም ሕፃናት ቀን የሕፃናትን መብቶችና ደኅንነትን ለማክበር፣ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የሕፃናትን ድምፅ ለማጉላት ያለመ ነው ።
ቀኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀን ተብሎ እንዲከበር የተወሰነው እ.አ.አ በ1954 በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ነው።
ኢትዮጵያም በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቷ ውስጥ በኢኮኖሚ መነቃቃት ላይ ያተኮሩ እና ለልጆች ምቹ የሆኑ የመጫወቻ ሥፍራዎችን የያዙ የከተማ ፕላን ላይ ቅድሚያ ሰጥታ በመሥራት ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ በፕሮጀክቶቿ ውስጥ የመጫወቻ ቦታዎችን በማካተት የአንድ ሀገር እድገት የሚለካው በመንገዶቿ እና በህንፃዎቿ ብቻ ሳይሆን በልጆቿ ደህንነት እና ደስታ መሆኑን እያሳየች ነው።
እነዚህ የመጫወቻ ሥፍራዎች ከመዝናኛነት ባሻገር ለልጆች ጤናማ እድገት አበርክቷቸው የጎላ ነው።
በዓለም ለ36ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20 ኛ ጊዜ የተከበረው ዕለቱ የሕፃናት መብት፣ ተጠቃሚነት እና ደህንነትን ለማስከበር ከሚከወኑ ተግባራት በተጨማሪ ዓለም አቀፉን የሕፃናት ቀን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሁነቶች ተከብሯል።
በሴራን ታደሰ