ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር አቻቸው ሎውረንስ ዎንግ ጋር በመሆን የሲንጋፖር የልማት ጉዞ ልምዶችን አስመልክቶ በተሰናዳ ወግ ላይ ተካፍለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት፤ የሲንጋፖርን ስኬት እና ትምህርት የሚሰጡ የልማት ጉዞ ልምዶችን ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር “የሀገር ግንባታ፣ አለማትን ማገናኘት” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ወግ ተካፍለናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በሀገር ግንባታ፣ በአመራር ዘዴ፣ በኢኮኖሚ ለውጥ እና በጂኦፖለቲካ ላይ ላካፈሏቸው ሀሳቦችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#EBC #EBCdotstream #Ethiopia #PMAbiy #Singapore