Search

9ኛው ኦዳ አዋርድ ትኩረቱን በሙዚቃው ዘርፍ ላይ አድርጓል

ማክሰኞ ኅዳር 16, 2018 53

9ኛው ኦዳ አዋርድ የፊታችን ኅዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

አዋርዱ ለሀገር ብሎም ለአፍሪካ ገጽታ ግንባታ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ባህላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ሚናው የጎላ መሆኑን የኦዳ አዋርድ አዘጋጅ በሻቱ ቶለማሪያም ገልጻለች።

በሻቱ ቶሎማሪያም መልቲ ሚዲያ ከውጭ ጉዳይ፣ ባህልና ስፖርት እንዲሁም ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው 9ኛው ኦዳ አዋርድ በዚህ ዓመት በሙዚቃ ዘርፍ ላይ ብቻ በማተኮር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚሁ መሠረት በዘንድሮው ኦዳ አዋርድ ከሀገር ውስጥ በ6 ዘርፎች 30 እጩዎች ቀርበው ከነዚህ መካከል 6 አሸናፊዎች ተለይተው ይሸለማሉ፤ ዘርፎቹም የሚከተሉት ናቸው ተብሏል፦

1. የሕይወት ዘመን ተሸላሚ

2. የዓመቱ ምርጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት

3. የዓመቱ ምርጥ ቪዲዮ ከሊፕ

4. የዓመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊት

5. የዓመቱ ምርጥ ወንድ ድምፃዊ

6. የዓመቱ ምርጥ ሀገርኛ ዘፋኝ

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ መሆኗ ከወዲሁ ይፋ ተደርጓል።

የተቀሩት እጩዎች ለሽልማት የሚበቁት ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ምርጫ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በኤልሻዳይ ወንድማገኝ

#ebcdotstream #ODAAward2025 #9thODAAward

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: