Search

የቡና ቱሪዝም

ማክሰኞ ጥር 19, 2018 85

ቡናን ለቱሪዝም ግብዓትነት ለማዋል እየሠራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

በመላው ዓለም ያሉ የቡና ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ እንዲተምሙ አስቻይ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ ሀገር አቀፍ የቡና ቱሪዝም ልማት ሴሚናር በጅማ ከተማ ተካሂዷል።

ሴሚናሩ የቱሪዝም ሚኒስቴር ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

የመደመር መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት ዘርፉ በፍጥነት እያደገ መምጣቱ በመድረኩ የተወሳ ሲሆን፤ ቡናን የዓለም አቀፍ ቱሪስቶች የፍሰት ማዕከል ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል።

ቡና አብቃይ በሆኑ ኮሪደሮች የቡና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ የቡናን ታሪክ እና ባህል ለቱሪዝም ግብዓትነት ለማዋል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በሚኒስቴሩ የቱሪስት መስህብ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ሙሳ ከድር ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ በበኩላቸው፥ የቡና ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ገቢ ከማግኘት ባሻገር የቱሪስት መስህብ በማድረግ ተጨማሪ ጥቅም እንዲያመጣ መሥራት ይገባል ብለዋል።

በራሄል አብደላ

#EBCDotstream #Ethiopia #Tourism #CoffeeTourism