በአዲስ ዓመት መባቻ እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ላይ ቢቻል ከጠረጴዛ ስር ሆኖ 12 የወይን ፍሬዎችን መብላት ጥሩ ዕድል ሊያመጣልዎ ይችላል።
ይህ ልማድ በስፔን ‘ላስ ዶሴ ኡቫስ ዴ ላ ሱዌርቴ’ (አስራ ሁለቱ ዕድለኛ ወይኖች) በመባል በደንብ ይታወቃል።
ስፔናውያን ታዲያ በአዲስ ዓመት መባቻ እኩለ ሌሊት ላይ የዓመቱ የመጀመሪያ ደቂቃ ከማለፉ በፊት (12፡01am ከመሆኑ በፊት) 12 የወይን ፍሬዎችን ይበላሉ።
12 የወይን ፍሬዎች የዓመቱን 12 ወራት ይወክላሉ፤ ለእያንዳንዱ ወር 1 የወይን ፍሬ እንደማለት ነው።
የአዲሱ ዓመት ሰዓት ወደ 12፡01am ከመቀየሩ በፊት አስራ ሁለቱን የወይን ፍሬዎች በልቶ መጨረስ ግድ ነው፤ ይህ ከመሆኑ በፊት ደቂቃው ከ01 መሙላት የለበትም።
ይህን ማድረግ ከሌሎች መልካም ዕድሎች በተጨማሪ ጥሩ የፍቅር አጋር ያመጣል ተብሎ ይታመናል።
ይህን ያደረገ ዓመቱን ሙሉ መልካም ዕድል ይገጥመዋል ብለውም ስፔናውያን እንደሚያምኑ የዘገበው ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ነው።
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እኩለ ሌሊት ላይ ከጠረጴዛ ስር ተቀምጠው ወይኖቹን እየተመገቡ የተለያዩ ቪዲዮዎችን ያጋራሉ።
በቢታንያ ሲሳይ
#EBC #ebcdotstream #Spain #newyear #12grapes #ritual