Search

በተቀየረ የሥራ ባህል፣ በኃላፊነት ስሜት እና በመደመር በመሥራት ሰላምን ማረጋገጥ እና ልማትን ማፋጠን ይገባል - አቶ ጥላሁን ከበደ

ረቡዕ ኅዳር 17, 2018 50

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው የመደመር ፍልስፍና ለኢትዮጵያ ስብራቶች ፍቱን መፍትሔ መሆኑን፤ መዳረሻችንም ሁለንተናዊ ብልጽግና እንደሆነ ገልጸዋል።

በመደመር ፍልስፍና የውስጥ አቅሞችን በመመልከት፣ አብሮ በመሥራት፣ ስህተትን በማረም የገጠመንን ስብራት መጠገን ብሎም የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል ማቃናት እንደምንችልም አብራርተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ የውስጥ አንድነትንማጠናከር ከመንግሥት ጎን መቆም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በተቀየረ የሥራ ባህል፣ በኃላፊነት ስሜት እና በመደመርመሥራት ሰላምን ማረጋገጥ እና ልማትን ማፋጠን እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሥራድልንመፍጠር እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አንስተዋል።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ፣ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት እና ልሎች ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ከማንሰራራት ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና እየተሸጋገረች መሆኑን አመላካች ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመደመር የሀገራችንን ማንሰራራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አሳክተን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንደምናደርጋት ጥርጥር የለውም ነው ያሉት።

በቢታንያ ሲሳይ

#ebcdotstream #medemer #prosperity