Search

ኮፕ 32ን በስኬት ማስተናገድ ትልቅ ትሩፋት ያስገኛል - ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

ሓሙስ ኅዳር 18, 2018 39

የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለሚመራው የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጻ አድርገዋል።
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ኮፕ 32 ጉባኤ ሀገሪቱ እስካሁን በተለያየ ደረጃ ስታከናውናቸው ከነበሩ ዓለምአቀፍ ጉባኤዎች የተለየ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮፕ 32 ጉባኤ በውስጡ አየር ንብረት ለውጥን ማዕከል ያደረጉ በርካታ የጎንዮሽ ስብሰባዎች እና ውይይቶች የተካተቱበት ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
ኮፕ 32 ከሀገርም አልፎ አህጉራዊ ፋይዳ ያለው ጉባኤ መሆኑንም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በተናበበ እና በተቀናጀ መልኩ ጉባኤውን በማዘጋጀት አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተጎጂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሔ አካልም ናት የሚለውን ማስገንዘብ እንደሚገባም ገልጸዋል።