Search

ወጣቱ ሚዛናዊ አስተሳሰብን በማዳበር ለሀገሩ ልማት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል - ከንቲባ ከድር ጁሀር

እሑድ ኅዳር 21, 2018 152

የአፍሪካ የወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር "የተለወጠ የወጣቶች የሥራ ባህል፣ ለኢኮኖሚ እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ ተካሂዷል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ወጣቱ ከስሜት ይልቅ በሃሳብ የበላይነት በማመን እና ሚዛናዊ አስተሳሰብን በማዳበር ለሀገር ብልፅግና ሚናውን ሊወጣ ይገባል።
ወጣቱ ለሀገር እድገት እና ልማት ምሰሶ በመሆኑ በኃላፊነት ስሜት ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራት ላይ መሳተፍ እንዳለበትም አሳስበዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ በበኩላቸው፤ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ለወጣቶችና ሴቶች ልዩ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።
መንግሥትም ይህንን ለማረጋገጥ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ረቂቅ ፖሊሲ እና የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በእውቀት፣ በክህሎት እና በሥነ-ምግባር የታነጸ እንዲሁም አገር ወዳድና ሥራ ፈጣሪ ትውልድ ለመፍጠር ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።
 
ቴዎድሮስ ታደሰ