በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪ እየሆነች የመጣችው ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂያዊ ደረጃ ማሳደጓ ሁለቱም ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተሰሚነት የሚጨምር ነው ሲሉ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ ሙሉጌታ ጌጡ (ዶ/ር) ገለጹ።
መሪ ተመራማሪው ከኢቲቪ 57 ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ለመቀላቀል ጥያቄዋን ስታቀርብ ሕንድን ጨምሮ የመስራች ሀገራቱን ሙሉ ድጋፍ ማግኘቷ፣ የምትከተለው የሰላማዊ ዲፕሎማሲ መንገድ ውጤት ነው ብለዋል።
ከ70 ዓመታት በላይ የዘለቀው የኢትዮጵያ እና የሕንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱንም ዶ/ር ሙሉጌታ አንስተዋል።

ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር የሚስማማ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ መርህ ያላት ሀገር ናት ያሉት ተመራማሪው፤ ሁለቱ ሀገራት አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የያዙትን ተመሳሳይ አቋም በአብነት ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ እና ሕንድ ከዚህ በኋላ በሚኖሩ ዓለም አቀፍ ሁነቶችም የጋራ አቋም እንደሚያራምዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ በነበራቸው የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ግልፅ ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#EBCdotstream #Ethiopia #India