በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ጭጋጋማ እና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ እንዳጋጠመው የጠቀሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ከሚቲዎሮሎጂ ባገኘው መረጃ መሠረት ይህ የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት እንደሚቀጥል ጠቁሟል።
በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለማቋረጥ መገደዱን ገልጾ፤ የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከል እና በረራዎችን መቀጠል እስከሚችል ድረስ መንገደኞች እንዲታገሱ ወይም አስቸኳይ ጉዞ የሚያደርጉ መንገደኞች ሌላ የጉዞ አማራጭ እንዲጠቀሙ በአክብሮት አሳውቋል።
የስታር አላየንስ አባል የሆነው አየር መንገዱ በአየር ፀባይ ምክንያት የተስተጓጎሉ በረራዎች ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደተመለሱ ለመንገደኞች የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ፤ በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ መጉላላቶች ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል።