Search

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ይፋ ሆኗል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ታኅሣሥ 11, 2018 114

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ይህን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ዛሬ በይፋ ማስጀመራቸውን አብስረዋል።

የስትራቴጂው ቁልፍ መሠረታዊ ትልሞች፥ ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎች እናተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።

እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የሕዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ሥራ የሚከናወን መሆኑን ጠቁመው ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ሥራዎች የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ገልጸዋል።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #AbiyAhmedAli #DigitalEthiopia # DigitalEthiopia2030