Search

"የሕዝብ እርካታን የሚጨምር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስልትን መከተል ይገባል" - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ሰኞ ታኅሣሥ 13, 2018 35

የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስልት ፈጣን፣ ተደራሽ፣ እመርታ የሚያመጣ እና የሕዝብ እርካታን የሚጨምር እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሳሰቡ።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ይፋ ሲደረግ ስትራቴጂው በመደመር መንግሥት እይታ መሠረት ፈጠራን፣ ፍጥነትን እና እመርታን ለማምጣት እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የማደግ ፍላጎት እና የማደግ አቅም ያላት ሀገር ናት ያሉት አቶ ተመስገን፤ የሚያስፈልገን የማደግ ፍላጎታችንን እና የማደግ አቅማችንን የሚያገናኝ ስልት ነው ብለዋል።
የዲጂታልን ዓለም ዕድሎች በመጠቀም አዳዲስ ስልቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ አሠራሮችን እና ግንኙነቶችን መፍጠር እንደሚገባም አመላክተዋል። ይህም አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እና አጠቃቀሞችን መፍጠርን ያካትታል ሲሉ አስረድተዋል።
አንድን የሥራ ሒደት ለማከናወን የሚወስደውን የሰው ኃይል፣ ጊዜ፣ ጉልበት እና ቁሳቁስ በመቀነስ እንዲሁም በመቆጠብ፤ አገልግሎትን እጅግ በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን ፍጥነት ወሳኝ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
የዲጂታል ዘርፍ ዋነኛው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ እና የብልጽግና መዳረሻ መንገድን ለማሳጠር የሚያስችል መሆኑን በማመን፣ መንግሥት በትኩረት እየሠራበት እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
 
በላሉ ኢታላ