Search

ከጥር 23 ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀምና ማምረት በህግ እንደሚያስቀጣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ

ማክሰኞ ታኅሣሥ 14, 2018 184

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከጥር 23 ጀምሮ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በሚያመርቱ እና በሚጠቀሙ ላይ የህግ የተጠያቂነት ድንጋነጌዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ አስታውቋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የፕላስቲክ ክልከላን የሚደነግገው አዋጅ ለአምራቾች ከተሰጠው የ6 ወራት የሽግግር ጊዜ  በኋላ ከጥር 23 ቀን 2018 ጀምሮ አዋጁ ተግባራዊ እንደሚደረግም ባለስልጣኑ ገልጿል።

በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በዚሁ ወቅት፤  ባለስልጣኑ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ መንግስት የከተሞችን ደረጃ ለማሳደግ እየሰራ ያለውን የልማት ስራ ሁሉም ሊደግፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራ፣ የወንዝ ዳርቻ እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ለመደገፍ አንድ ጊዜ ተጠቅመን የምንጥላቸው የፕላስቲክ ምርቶች ለሚካሄዱየ ልማት ስራዎች እንቅፋት ስለሚሆኑ አዋጁን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ።

ቀደም ሲል በዚሁ የፕላስቲክ ምርቶች ማምረት ላይ ተሰማርተው የቆዩ አምራቾችም ወደ ሌላ ዘርፍ መሰማራት እንዲችሉ በጋራ ሲሰራ መቆየቱንም ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል።

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ማስገባት እና መሸጥን በህግ እንደሚከለክል ተገልጿል፡፡

በኤዶም አማረ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #plastic_waste #environmental_protection