Search

ኢቢሲ ለቤቶች ድራማ ስኬት የጀርባ አጥንት ነው - አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ

ቅዳሜ ታኅሣሥ 18, 2018 127

የቤቶች ተከታታይ ድራማ መሪ ተዋናይ እና ፕሮዲውሰር አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ፤ ድራማው ላለፉት 13 ዓመታት ሳይቆራረጥ 525 ክፍሎችን ለሕዝብ እንዲያደርስ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጠንካራ የጀርባ አጥንት ሆኖ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገለጸ።
አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ በቤቶች ድራማ 13ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ እንደገለጸው፤ ኢቢሲ ላለፉት 60 ዓመታት ልዩ ልዩ አዝናኝ፣ አስተማሪና ታሪካዊ ሥራዎችን ለሕዝብ በማቅረብ ትልቅ ባለውለታ ነው።
 
ለቤቶች ድራማም ኢቢሲ በተቋመ ደረጃ እገዛ በማድረግ፣ በማበረታታትና ከጎን በመቆም ላሳየው ቁርጠኝነት ላቅ ያለ ምስጋና እንደሚገባ አርቲስቱ ገልጿል።
በኢቢሲ በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማዕረግ የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘላለም እንዳሻው በበኩላቸው፤ እንደ ቤቶች ያለ በጽናት የሚዘልቅ፣ ምሳሌ የሚሆንና ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች መፍለቂያ ከሚሆን ተቋም ጋር ኢቢሲ በቀጣይም በጋራ ይሠራል ብለዋል።
ኢቢሲ በመዝናኛው ኢንዱስትሪ ያለውን አበርክቶ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
 
በወንድወሰን ሞላ