የቁልቢ ቅዱስ ገብርዔል የንግስ በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተገኙበት ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።
በየዓመቱ ታህሳስ እና ሐምሌ 19 በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በሚከበረው የንግስ በዓሉ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ተማሪዎች እና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የመጡ ምዕመናን ታድመዋል።
ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ስፍራው ያቀኑ ምዕመናን በዓሉን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በድምቀት እያከበሩ እንደሚገኙ ለኢቲቪ ተናግረዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ