በኢትዮጵያ የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ሆኖ የዘለቀው ግብርናው ብዙ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ሆኖ ነው ዘመናትን የተሻገረው።
ይህን ችግር ለመፍታት በተለይ ከ2010 በኋላ የኢትዮጵያን ግብርና በመለወጥ በዓመት አንዴ ከማምረት እና ከዝናብ ጥገኝነት እንዲላቀቅ የተጀመሩ ሥራዎች ውጤት አስገኝተዋል።
በዚህም ዘመናዊ የግብርና አሠራሮች የኢትዮጵያን ግብርና በመለወጥ፣ አርሶ አደሮች ምርትን እንዲያሳድጉ፣ ቅልጥፍናን እንዲያሻሽሉ እና ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እንዲላመዱ እያገዛቸው መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመላክታል።
ከተሻሻሉ ዘሮች ወደ ተሻለ መስኖ እና ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራዎች በገጠሩ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለውን ኑሮ እያጠናከሩ ይገኛሉም።
ግብርና የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ ቀጥሏል፣ ዕድገትን በማነሣሣት፣ ብልጽግናን በመደገፍ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ጉልሕ ሚና አሁንም አለው።