Search

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

ማክሰኞ ታኅሣሥ 28, 2018 180

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል 2018 . የልደት በዓል መልዕክት

በስመ አብ፣ በስመ ወልድ፣ በስመ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን!

ከሁሉ አስቀድሜ በሀገራችን በኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገራት ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ እንኳን 2018 . የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያልኩ በራሴና በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ስም በዓሉ የደስታና የፍቅር ይሆንላቸሁ ዘንድ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ።

ልዑል እግዚአብሔር 700 ዓመታት በፊት በነቢዩ ኢሳይያስ በኩልሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል.... ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም ያለው ቃሉ በአንድያ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍጻሜ በማግኘቱ፤ የእግዚአብሔርን ይቅርባይነት እና ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር እያሰብን ይበልጥ እንድናመሰግነው ያደርገናል (ኢሳ. 96) ፡፡

 ስለሆነም ለእግዚአብሔር ለአምላካችን ክብርና ምስጋና ይሁን፡፡

እንግዲህ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን በመላክና የኃጢአታችንን ዋጋ በመስቀል ላይ እንዲከፍል በማድረግ ከራሱ ጋር እንዳስታረቀን ሁሉ፤ እኛም ለሌሎች ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ ፍቅርና ምህረት እንድንመሰክር ታዝዘናል (2ቆሮ 518-20)፡፡

ስለሆነም ሰው ሁሉ ከአምላኩ፤ ከራሱና ከእርስ በርሱ ጋር ይታረቅ ዘንድ ያላንዳች መሰልቸት ወንጌልን ማስተማር ግድ ይለናል፡፡ የታረቀ ሕዝብ ከዕድገት ወደ ላቀ ዕድገት ከመሸጋገር የሚያግደው ነገር ስለሌለ ልዩነቶችን በእርቅ በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እንተጋ ዘንድ የዘወትር መልዕክታችን ነው፡፡

በተለይም ለሰላሙ ፍጻሜ የሌለውን፤ የሰላም አምላክ የምናመልክ ሁላችን ፍቅርንና ሰላምን ከማስተማርና ከማወጅ ውጭ ሌላ መለኮታዊ ተልዕኮ የለንም፡፡ ሆኖም ያልታረቀ ማስታረቅ ስለማይቻለው በቅዲሚያ እኛ ራሳችን ታርቀንና በመካከላችንም እውነተኛ ሰላምን አስፍነን፤ መልካም ምሳሌነታችን ጎልቶ እንዲታይ ለማድረግ ጊዚያችንን በአግባቡ

እንጠቀምበት፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚታዩትን የልማት ሥራዎች ስንመለከት፤ ችግሮቻችንን በሰላማዊ መንገድ ፈትተን፣ ለጋራ ጥቅም ብንረባረብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ዕደገት ማስመዝገብና ከድህነት መላቀቅ ይቻለናል፡፡

ለዚህም ጠንካራ ሕዝባዊ አንድነት በመገንባት፤ ተደማምጦና ተከባብሮ፣ በሰላምና በፍቅር ለመኖር አስፈላጊውን

ሁሉ ከማድረግ መቆጠብ የለብንም፡፡

አንድነት ጠላትን ድል ማድረጊያ ብርቱ መሣሪያ ስለሆነ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን፣ ጸንተን በአንደነት በመቆም ከራሳችን አልፎ፣ ሌሎችየሚማሩበት ታሪክ እንሠራ፡፡

በመጨረሻም የልደትን በዓል ስናከብር፤ በልዩ ልዩ ምክንያት በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች የደስታችን ተካፋዮች ይሆኑ ዘንድ፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በመለገስ እንዲሆን በጌታ ፍቅር አሳስባለሁ፡፡

እግዚአብሔር ህዝባችንን ይባርክ! ሰላሙንም ያብዛልን! አሜን

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል