የ1447ኛው የዒድ ሷላት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተሰግዶ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በኢድ ሷላት ሥነ-ሥርዓት ላይ የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጠሃ ሃሩን ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ሀገር እንድትሆን እያንዳንዱ ዜጋ በአብሮነት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
የ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ላይ የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጠሃ ሃሩን ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ሀገር እንድትሆን እያንዳንዱ ዜጋ በአብሮነት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በቅዱሱ ረመዷን ያካበታቸውን የትዕግሥትና የጽናት እሴቶች ከወሩ መጠናቀቅ በኋላም በተግባር ሊያሳያቸው እንደሚገባም ገልጸዋል።
ኢማሙ በመልዕክታቸው ዘካተል ፊጥርን በሰዓቱ ለተቸገሩ ወገኖች በማድረስ ድሆች የበዓሉ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል።
በተጨማሪም ምእመናን ከሐሰት፣ ከማጭበርበርና ከበደል በመራቅ በንግድም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነት ውስጥ እስላማዊ ታማኝነትን ሊያሳዩ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዓሉ በጁምዓ ቀን መዋሉ ልዩ በረከት እንዳለው የጠቆሙት ሀጂ ጠሃ፤ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ዱዓ በማድረግና የሸዋልን ስድስት ቀናት በመጾም መንፈሳዊ ጥንካሬን ማሳደግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በላሉ ኢታላ