Search

በትውልድ መስዋዕትነት የሚገነቡ የልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያረጋግጡ ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ መጋቢት 15, 2018 50

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በትውልድ መስዋዕትነት የሚገነቡና የዜጎችን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) "ከተማ፣ ከተሜነት፣ ክትመት እና የኮሪደር ልማት በሚል መሪ ሐሳብ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

እንደ ከተማ መልሶ ማልማትና ክላስተር እርሻ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሲከናወኑ ለጊዜው የሚታዩ ተግዳሮቶች ለረጅም ጊዜ ስኬት ሲባል የሚታለፉ መሆናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የልማቱ ድምር ውጤት በሀገርም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ ዕድገት እንጂ ውድቀት እንደማያመጣ አስረድተዋል።

የሀገር ግንባታ በዋዛ ፈዛዛ እንደማይሳካና የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ የበቁት በዜጎቻቸው "ደም እና አጥንት" መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ዋናው ዓላማ ለሕዝብና ለሀገር ብልጽግና መሥራት መሆኑን አስገንዝበዋል።

አሁን የሚታዩ ችግሮች ጊዜያዊ ቢሆኑም፣ በረጅም ጊዜ ሂደት ኢትዮጵያ ስታድግ የማይጠቀም ዜጋ እንደማይኖርና እያንዳንዷ ሰከንድ የኢትዮጵያን ብልጽግና በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንደምትውል አረጋግጠዋል።

በቢታኒያ ሲሳይ

#EBC #Ethiopia #Development #NationalBuilding #Prosperity #PMAbiyAhmed