Search

የ50 ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ባለ 27 ወለል ህንፃ አስመረቀ

ቅዳሜ መጋቢት 19, 2018 104

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት በሆነው ሱማሊ ተራ አካባቢ ያስገነባውን እጅግ ዘመናዊ ባለ 27 ወለል (3B+G+23) ሁለገብ ሕንፃ ዛሬ አስመርቋል።
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትርና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) ተከናውኗል።
የ50 ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን በተለያዩ ኩነቶች እያከበረ የሚገኘው ኮርፖሬሽኑ፣ ይህንን ዘመናዊ ሕንፃ ወደ ስኬት በተሸጋገረበት ወሳኝ ወቅት ላይ እውን ማድረጉ ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል።
ሕንፃው ለመኖሪያና ለንግድ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የተገነባ ሲሆን፣ በዲዛይኑም ሆነ በአጨራረሱ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የሕንፃ ግንባታ ግብዓቶችንና ቴክኖሎጂዎችን የተጠቀመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ በታሪካዊው የሱማሊ ተራ አካባቢ የቆመው አዲስ አሻራ፣ የከተማዋን ውበት ከመጨመር ባለፈ ለንግድና ለመኖሪያ ምቹ የሆኑ አማራጮችን በማቅረብ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የኮርፖሬሽኑን ሽግግርና የዕድገት ጉዞ ከማሳየኡም በላይ ባለፉት ዓመታት የጀመራቸው ግዙፍ የቤት ልማት ፕሮጀክቶች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ማሳያ ሆኖል።
በሀብታሙ ተክለሥላሴ