Search

ከግማሽ ክፍለ ዘመን ጉዞ እስከ አዲሱ ምዕራፍ፤ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ታሪካዊ ዐውደ ርዕይ ተከፈተ

ቅዳሜ መጋቢት 19, 2018 134

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረውን የጉዞ ታሪክ የሚያሳይ ልዩ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በይፋ ተከፍቷል።
ኤግዚቢሽኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዓለምፀሀይ ጳውሎስ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና ከሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን መርቀው ከፍተውታል።
በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ያለፈባቸውን የተለያዩ የከፍታ እና የዝቅታ ምዕራፎች፣ እንዲሁም ተቋማዊ ለውጦችን በዝርዝር የሚያመላክቱ ታሪካዊ ፎቶግራፎች ለዕይታ ቀርበዋል።
በተለይም ተቋሙ ከሀገራዊ ለውጡ ማግሥት እያሳየ የሚገኘውን አስደናቂ ስኬት ተከትሎ "በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ" በሚል መሪ ቃል እያከናወናቸው ያሉ የሪፎርም ሥራዎች እና ግዙፍ የልማት እንቅስቃሴዎች የኤግዚቢሽኑ ዋነኛ አካል መሆናቸው ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በተሻለ ቁመና ላይ ሆኖ የተቋሙን ገፅታ የሚቀይሩ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል።
በሀብታሙ ተክለሥላሴ