Search

ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ ንፁህ ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ ደርሳለች - ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

ዓርብ ሚያዝያ 02, 2018 210

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (/) ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ከፍተኛ ሥራ እያከናወነች መሆኗን ገለፁ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት በቪዬና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኢነርጂ እና አየር ንብረት ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

አፍሪካ ያላትን ሰፊ የታዳሽ ኢነርጂ እምቅ አቅም በመጠቀም እና በወሳኝ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር፣ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪያል እድገት ለመሸጋገር ያላትን ልዩ እድል አጉልተው ገልጸዋል።

የኢነርጂ ተደራሽነት ውስንነት፣ የመሠረተ ልማት ክፍተቶች እና የገበያ ተደራሽነት እጥረትን ጨምሮ ያሉ እንቅፋቶችን በአስቸኳይ መፍታት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ማመንጫዎች ላይ እያከናወነች ያለውን መጠነ ሰፊ ተግባር ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ ሀገሪቱ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስፋፋት በአሁኑ ወቅት 95 በመቶ በላይ ንፁህ ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ መድረሷን ጠቁመዋል።

ይህም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ላይ ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ከፎረሙ ጎን ለጎን ከኦስትሪያ እና ደቡብ ሱዳን አቻዎቻቸው ጋር በሁለትዮሽ እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

#EBC #Ethiopia #RenewableEnergy #ClimateAction #ViennaForum #GedionTimothewos #GreenEconomy