በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የቁሳቁስ ስርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአሶሳ ሆሃ እና የአሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ለየምርጫ ጣቢያዎቻቸው የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ሥራ እየሠሩ ነው።

የአሶሳ ሆሃ የምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ እሱባለው ንጋቱ እና የአሶሳ መገሌ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንዳሉት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅድመ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ እስከ ግንቦት 22 ቀን ድረስ በሁሉም ጣቢያዎች ቁሳቁሶችን አሰራጭተው ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
እነዚህን የምርጫ ክልሎች ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሁሉም አካባቢዎች ከሚገኙ ማዕከላት ወደ ሁሉም ጣቢያዎች ቁሳቁሶችን በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።
በጀማል አሕመድ