በአምቦ ከተማ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ወደየምርጫ ጣቢያዎቹ እየተሰራጩ መሆኑን የከተማው ምርጫ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምስጋና ሰዴሳ እንዳሉት፣ ለሂደቱ በሁሉም ረገድ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል፡፡

በዚህም መሰረት የድምፅ መስጫ ወረቀትን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች ወደ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ 42 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ ዞኑን ጨምሮ በጠቅላላው 105 ጣቢያዎች እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
የከተማው የቁሳቁስ ስርጭት ዛሬ ተጠናቅቆ፣ ነገ ማለዳ ወደ ዞኑ ሌሎች አካባቢዎች እንደሚቀጥልም ኃላፊው አክለው ተናግረዋል፡፡
በእየሩሳሌም ሽመልስ