በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዳውሮ ዞን ነዋሪዎች በምርጫ ካርዳቸው ሀገር የሚያስተዳድር መንግሥት ለመምረጥ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡
በዞኑ የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ለኢቢሲ በሰጡት አስተያየት በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ የወሰዱት ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተገቢው እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ ባለፈ፣ ሀገር የሚያስተዳድረውን መንግሥት ለመምረጥ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡
ስለሆነም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገር እና ለሕዝብ የሚጠቅመውን በመምረጥ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በሀገር ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ይበልጥ ለማጎልበት ሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባውም ነዋሪዎቹ አብራርተዋል፡፡
በሰለሞን ባረና