Search

አዲስ የሕግ ትርጉም፤ የቦታ ባለመብትነት እና የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ

ሰኞ ሚያዝያ 19, 2018 112

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት፣ በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ቢሰጥ ለቦታው ባለመብትነት በተመለከተ ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረውን የሕግ ትርጉም በመለወጥ አዲስ ውሳኔ አሳልፏል።
ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ይህ ችሎት ከመጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የሕግ ትርጉም የሰጥቷል።
በዚህም መሠረት በአንድ ባለይዞታ ሊመዘገብ የሚገባን የከተማ ይዞታ ከአንድ በላይ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ ለተለያዩ ሰዎች ተደርቦ ተሰጥቶ ሲገኝ ለቦታው ባለመብትነት ቅድሚያ የሚሰጠው መጀመሪያ ያስመዘገበው ሰው ነው በሚል ተተርጉሟል፡፡
ይህ አዲስ ውሳኔ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 186946 በአንድ የመሬት ይዞታ ላይ ካርታ ተደርቦ ቢሰጥና በኋላ ካርታ የተሰጠው ሰው መሬቱ ላይ ቤትና ንብረት ካፈራ መጀመሪያ ካርታ ከወሰደው ይልቅ ንብረት አፍርቶ ያለው ባለመብት ሊሆን ይገባል የሚለውን አስገዳጅ ትርጉም እና መሰል መዝገቦች ላይ የተያዘው ተመሳሳይ አቋም ሙሉ በሙሉ የሻረ ነው።
ይህ ውሳኔ በከተሞች ውስጥ በይዞታ ማረጋገጫ ያልጸደቁ ነገር ግን ግንባታ ተገንብቶባቸው ግለሰቦች ለረጅም ጊዜ የኖሩባቸው ቤቶች ላይ የሚነሱ ክርክሮችን ለመቋጨት ትልቅ የሕግ አቅጣጫ መሆኑ ተመልክቷል።
በብርቱካን አስናቀ