ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና የቆዩ ሀገራዊ ስብራቶችን በዘላቂነት ለመጠገን ያለመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት በተለያዩ የትግበራ ምዕራፎች ውስጥ አልፎ በአሁኑ ወቅት ዋናው የምክክር መድረክ በስፋት እየተካሄደ ይገኛል።
ከየኅብረተሰብ ክፍሉ የተወከሉ በርካታ ተሳታፊዎች በአንድ አዳራሽ ተሰባስበው በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት እየመከሩ ይገኛሉ።
ከዚሁ ሂደት ጋር ተያይዞ አስተያየታቸውን የሰጡት የምክክሩ ተሳታፊ እንደገለጹት የምክክሩ አካሄድ እና አጠቃላይ እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ሂደቱ እስከ ዛሬ ስንሰማቸው እና ስናያቸው የነበሩ የተዛቡ አሠራሮችን እና አመለካከቶችን ለማስተካከል እንዲሁም ለቀጣዩ የሀገር ግንባታ ሂደት ፅኑ መሠረት ለማስቀመጥ ትልቅ አጋጣሚ ይዞ መምጣቱን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል።
የሕዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ተሳታፊዎቹ በመድረኩ እየተነሱ እና ውይይት እየተደረገባቸው ያሉ ሀሳቦች እጅግ ታላላቅና ሚዛናዊ እንደሆኑ ገልጸዋል።
በሂደቱም በርካታ ትላልቅና ስትራቴያዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ መቻሉን ጠቁመዋል።
አሁን እየተከናወነ ያለው የምክክር መድረክ ለነገይቱ የተሻለች ኢትዮጵያ ትልቅ ሀሳብ እና አጀንዳ ይዞ የመጣ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
ተሳታፊዎች በሃሳብ ልዕልና እና በሥልጡን ውይይት ለሀገራቸው ብሩህ ተስፋ መሠረት ለመጣል ያላቸውን ዝግጁነት እያረጋገጡም ይገኛሉ።
በሐና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: