የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና በቀድሞው የፖሊስ ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ላይ የጽኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ።
የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ ያቀረበውን የምርመራ መዝገብ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል "የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት" የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀት ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቲዎስ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እና በ4 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ወስኗል።
ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ሽመልስ ቶማስ ደግሞ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና በ1 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: