ለወጣቶች እና ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች፣ ሰላማዊ እና የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ሰፊ ውይይት እያደረጉ መሆናቸውን በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ወጣቶች ገለጹ።
ተመካካሪዎቹ እንደገለጹት መድረኩ ሁሉም ተሳታፊዎች በሚገባቸው ቋንቋ ሃሳባቸውን በነፃነት የሚያቀርቡበት እና የጋራ መግባባትን የሚያጠናክር ታሪካዊ አጋጣሚ ፈጥሯል።
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ከጋምቤላ እና ከድሬዳዋ የመጡት ወጣቶቹ የምክክሩ ሂደት ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ሙሉ በሙሉ አካታች መሆኑን ገልጸዋል።
በጉባኤው የተለያዩ አመለካከቶች ቢንፀባረቁም፣ በአብዛኛዎቹ የሀገር ግንባታ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እየተፈጠረ ይገኛል።
ይህ ምክክር ለረጅም ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ ሀገራዊ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት፣ የጋራ ራዕይን ለመቅረፅ፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ለማጠናከር እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ የተባበረችና የተረጋጋች ሀገር ለማሸጋገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: