Search

በሐረሪ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማጓጓዝ ሥራ ተጀመረ

ዓርብ ግንቦት 21, 2018 71

በሐረሪ ክልል ድምፅ ወደሚሰጥባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝ ሥራ ተጀምሯል።

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሐረሪ ክልል ምርጫ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ጌታቸው ቦጋለ እንደገለጹት፣ በክልሉ በሚገኙ የምርጫ ክልሎች እንዲሁም በአዳዲስ ስምንት ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል።

አስተባባሪው አክለውም በክልሉ በሚገኙ 2 መቶ 96 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ አስፈላጊውን የምርጫ ቁሳቁስ የማጓጓዝ ሥራ መጀመሩን ያነሱ ሲሆን፣ እያንዳንዱ የቅድመ ምርጫ ዝግጅት በተያዘው መርሐ-ግብር መሠረት በጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ መራጮች ግንቦት 24 ቀን የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ለኢቲቪ ተናግረዋል።

 

ቴዎድሮስ ታደሰ