Search

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጨረሻ ውጤት ማጠቃለያ

እሑድ ሰኔ 14, 2018 80

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋዊ ውጤት አሳውቋል።

በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች 94% እስከ 99% የሚደርስ ከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ ታይቷል።

በምርጫው ብልፅግና ፓርቲ በአብዛኛዎቹ የምርጫ ክልሎች በማሸነፍ አብላጫውን የምክር ቤት መቀመጫ ወስዷል።

ዋና ዋና የክልል እና ከተማ አስተዳደር የምርጫ ውጤቶች

አዲስ አበባ

ከተመዘገቡት 1,957,676 መራጮች ውስጥ 96% ድምጽ ሰጥተዋል። 23 የምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ ብልፅግና 20 ኢዜማ 2 እና 1 የግል እጩ (አበበ ገመቹ ሌንጫ) አሸንፈዋል።

ኦሮሚያ

24,094,121 መራጮች በተመዘገቡበት ክልል 97% ተሳትፎ ተመዝግቧል። 173 መቀመጫዎች ብልፅግና 167ቱን አሸንፏል። ቀሪዎቹን 6 መቀመጫዎች 5 የግል እጩዎች እና 1 የአዲስ ትውልድ ፓርቲ እጩ ተከፋፍለዋቸዋል።

አማራ

ከተመዘገቡት 10,876,829 መራጮች 95% ድምጽ ሰጥተዋል። 130 መቀመጫዎች ብልፅግና 117 አግኝቷል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 6 የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ 3 እንዲሁም ሌሎች ፓርቲዎች (ኢዜማን ጨምሮ) ቀሪውን ወስደዋል።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ 33 መቀመጫዎች ብልፅግና 28ቱን ወስዷል። ኢዜማ 2 ሲያገኝ፣ 3 ሌሎች ፓርቲዎች እና 1 የግል እጩ እያንዳንዳቸው አንድ መቀመጫ አሸንፈዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 20 መቀመጫዎች ብልፅግና 17ቱን ሲወስድ፣ ኢዜማ፣ ነፃነትና እኩልነት፣ እና ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 1 መቀመጫ በየራሳቸው አግኝተዋል።

ሲዳማ፣ ሶማሌ እና ሌሎች ክልሎች

ሲዳማ፡ 16 መቀመጫዎች ብልፅግና 13 መድረክ 3 አሸንፈዋል።

ሶማሌ፡ 22 መቀመጫዎች ብልፅግና 19 ኦብነግ 1 እና 2 ሌሎች ፓርቲዎች እያንዳንዳቸው አንድ ወስደዋል።

አፋር፡ 8 መቀመጫ ብልፅግና 7 የአፋር ሕዝብ ፓርቲ 1 አግኝተዋል።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡ 9 መቀመጫ ብልፅግና 8 የጉሙዝ ሕዝብ ንቅናቄ 1 አሸንፈዋል።

ሀረሪ፡ 2 የምክር ቤት መቀመጫዎች ሲኖሩ ሁለቱንም ብልፅግና ፓርቲ ወስዷል።