Search

በጋምቤላ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተጀመረ

ዓርብ ግንቦት 21, 2018 64

በጋምቤላ ክልል በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚውሉ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ክልሎች ማጓጓዝ ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ተፈራ እንደገለጹት፣ ከቦርዱ ተልከው ትናንት ምሽት ክልሉ የደረሱት የምርጫ ቁሳቁሶች ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ 14 የምርጫ ክልሎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይነትም ወደ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮች የማጓጓዝ ስራው እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በሚፍታህ አብዱልቃድር