የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀናል የሚሉትን ወኪል ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ ምርጫው የዴሞክራሲ መሠረት እና ዋነኛ መገለጫ በመሆኑ፣ የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የአንድ ሰው ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ያነሱት ነዋሪዎቹ፣ አንድም የምርጫ ካርድ መባከን እንደሌለበትም አስገንዝበዋል።
ዘንድሮ የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በርካታ ፓርቲዎችን ያሳተፈ እና የፓርቲዎችም ማኒፌስቶ በስፋት የተደመጠበት በመሆኑ፣ የፓርቲዎችን አቋም ቀድሞ አውቆ ለውሳኔ ለመዘጋጀት እንደረዳቸውም ገልጸዋል፡፡
የእስካሁኑ የምርጫ ሂደት በስኬት መከናወኑን እና የድምፅ አሰጣጡም በተመሳሳይ መልኩ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
በእየሩሳሌም ሽመልስ