በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀናል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የድምፅ መስጫ ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ በዕለቱም ለሀገራችን ሰላም፣ ልማት እና ሁለንተናዊ ዕድገት ያመጣል የምንለውን ፓርቲ እንመርጣለን ብለዋል።

ድምፅ መስጠት የዜግነት ኃላፊነትን መወጣት መሆኑን ያነሡት ነዋሪዎቹ፣ የአንድ ሰው ድምፅ ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው በመገንዘብ፣ ዜጎች በሂደቱ ላይ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ ነዋሪዎቹ በትዝብታቸው አረጋግጠዋል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ