Search

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ

ማክሰኞ ግንቦት 25, 2018 118

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 . በከፍተኛ ንቃት እና ትዕግሥት ድምፃቸውን ስለሰጡ አመስግኗል።

በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስም በትዕግሥት እንዲጠብቁ እና ሌሎች አካላትም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ፤ ሕዝቡም ከመሰል መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ቦርዱ አሳስቧል።