ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ ባደረገው ምልከታና ክትትል ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ በሰጡት መግለጫ፤ ኮሚሽኑ በምርጫው ሂደት ላይ ታዛቢ ባለሙያዎችን በማሰማራት ሂደቱን በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን ገልጸዋል።
በዚህም ምርጫው የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ኮሚሽኑ ባደረገው ምልከታና ክትትል ማረጋገጡን ጠቅሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ለምርጫው ሂደት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በሙሉ በተገቢው መልኩ ተሟልተው መቅረባቸውን ጠቁመዋል።
በምርጫው ዕለት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ የታዩትን ረጃጅም ሰልፎች በተመለከተ፣ ኮሚሽኑ ለቦርድ ጥቆማ ማቅረቡን ጠቅሰው፤ ቦርዱም በቀረበለት ጥቆማ መሰረት የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰዱን ምባራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኮሚሽኑ በቀጣይም በድህረ-ምርጫ ሂደቶች ላይ ተከታታይ ክትትል እንደሚያደርግና በሂደቱ የሚያገኛቸውን ማናቸውንም ግኝቶች ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።