Search

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እየጎለበተ መምጣቱን ያሳየ ነው - የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ማክሰኞ ግንቦት 25, 2018 60

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እየጎለበተ መምጣቱን ያሳየ ነው ሲል የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።

የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ በለጠ ሲጌቦ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ተወጥቷል።

ለምርጫው በስኬት መካሄድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ በለጠ ተናግረዋል።

ምርጫው የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገርና ህዝብን ያስቀደሙበት እንዲሁም የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ጎልቶ የታየበት ነው ብለዋል።

አጠቃላይ የምርጫው ሂደት በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እየጎለበተ መምጣቱን ያሳየ መሆኑን አመልክተዋል።

የምርጫው ሂደት ሰላማዊና ነጻ ሆኖ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።