በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ግንቦት 24 የተካሄደውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማደራጀት እና ለመምራት ላደረገው ከፍተኛ ጥረት ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አድናቆቱን ገልጿል።
ኤምባሲው ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ጃፓን በምርጫ ሂደቱ ላይ ለተሳተፉት እጩ ተወዳዳሪዎች በሙሉ እንዲሁም ድምፃቸውን ለመስጠት ለቻሉ የኢትዮጵያ ዜጎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።
በተጨማሪም ጃፓን የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ሂደት ለመደገፍ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ በማድረጓ የተሰማትን ደስታ ገልጻለች።