49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ይከናወናል።
በስብሰባው መክፈቻ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቫር ጋቴቴ፣ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኤድዋርድ ቢዚማና፣ የአባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ሚኒስትሮቹ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ አጀንዳዎች እና የአፍሪካን አህጉራዊ ትስሰር ማፋጠን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።
የአጀንዳ 2063 አፈፃፀም የሚከታተለውን ኮሚቴ ሪፖርት እንዲሁም የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና በአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ወቅት ያሉ ስምምነቶችና የአሰራር ማዕቀፎች ያሉበትን የትግበራ ደረጃም ይገመግማሉ።
በተጨማሪም የ2026ቱን የህብረቱን የዓመቱ መሪ ሀሳብ የእስካአሁን የአፈጻጸም ሂደት ላይ እንደሚወያዩም ኢዜአ ዘግቧል።
49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እስከ ነገ ይቆያል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: