Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኖርዌይ አምባሳደር ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ተወያዩ

ረቡዕ ግንቦት 26, 2018 49

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ከሆኑት ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV Summit) ላይ በጋራ በምንሰራቸው ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

ከተማችን አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድ እና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተች እና ተመራጭ እየሆነች የመጣች በመሆኗ ይህንንም ጉባኤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እናሳካዋለን ሲሉም አክለዋል።