በ49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
በዚሁ መሠረት፣ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና (ዶ/ር) አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ መላኩ በዳዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
49ኛው የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ከሐምሌ 21 ጀምሮ ለሁለት ቀናት “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና አስተማማኝ የንጽሕና አጠባበቅ ሥርዓትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በጉባኤው ለመሳተፍ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድን አባላትም ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: