የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት መስፋፋት ዜጎች በስማርት ስልክ እና በኢንተርኔት ብቻ በቀላሉ የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት እንዲቻል ማድረጉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አብዮት ባዩ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ኢቢሲ በራሱ አቅም ያበለፀገውን መተግበሪያ በይፋ ባስመረቀበት ወቅት አብዮት ባዩ (ዶ/ር) "ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የዲጂታል ሚዲያው ሚና ምንድን ነው" በሚል በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
አብዮት ባዩ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው፤ የኢንተርኔት ተደራሽነት መስፋፋት ሚዲያዎች እንዲተጉ እና ተወዳዳሪነታቸው እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል፡፡
የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም መሰረታዊ የሚባሉትን ሲስተሞች በሀገራችን እንዲኖሩ በማድረግ ከፍተኛ ስራ አከናውኗል ያሉት አቶ አብዮት፤ የኔትዎርክ ሽፋኑ 99.4 በመቶ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
ሰው በሚኖርበት ማናቸውም የሀገራችን ክፍል ብንጓዝ አስተማማኝ የሆነ የኔትወርክ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ሲስተም መገንባት ተችሏል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
የመሰረተ ልማት መስፋፋት ዜጎች በስልክ ብቻ በቀላሉ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ ማድረጉን ያነሱት አቶ አብዮት፤ ኢቢሲ ይህን እድል በመጠቀም በራስ አቅም ያበለፀው የዲጂታል መተግበሪያ ወደ ብዙዎች ለመድረስ እንደሚያችለው ተናግረዋል፡፡
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#EBC #ebcdotstream #Digital_EBC #DigitalEthiopia #EBCApp