የአፍሪካ ህብረት በዓለም አቀፍ አጋሮች የሚሸፈነውን 80 በመቶ የበጀት ድርሻ በአባል ሀገራት መዋጮ መሸፈን እንዳለበት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ የሱፍ ገለጹ።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ መካሄድ በጀመረው 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
በስብሰባው "የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና አስተማማኝ የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣ የአህጉሪቱን መፃኢ እድል የሚወስኑ በርካታ አህጉራዊ ጉዳዮች እየተነሱበት ይገኛል።
በመድረኩ የህብረቱን የፋይናንስ አቅም ማደራጀት፣ የሽብርተኝነትን መስፋፋት መግታት እና የጤና ዋስትናን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።
በቶማስ ሀይሉ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: