ሕዝበ ሙስሊሙ ነገ አርብ ነሃሴ 9፣ 2017 ዓም የዑለማ ምርጫ እንደሚያካሂድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አብዱልአዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር) የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ የዑለማ ምርጫውን ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።
አካታች፣ አሳታፊ፣ ፍትሃዊ እና የሕዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት ያስጠበቀ ምርጫ ለማድረግም ሰፊ ሥራ መሰራቱን ገልፀዋል።
ሂደቱ በክላስተር ተከፋፍሎ የተመራ መሆኑን ያነሱት ሰብሳቢው፤ በሁሉም ክልል እና የከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ መስጂዶች ምዝገባ መከናወኑን እና bተለዩት ዘርፎች ላይ ነገ ምርጫው እንደሚካሄድ አንስተዋል።
ለምርጫው 13 ሚሊዮን 151 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል።
በትግራይ ክልል አመቺ ሁኔታ ባለመፈጠሩ የምርጫ አስፈፃሚ ቦርዱ በጠየቀው መሰረት ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰብሳቢው ተናግረዋል።
በሀብታሙ ተክለሥላሴ
#EBC #ebcdotstream #Election