Search

ባለፉት ዓመታት በተካሄደው ዘርፈ ብዙ ሪፎርም አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡- አቶ አደም ፋራህ

ረቡዕ ሐምሌ 29, 2018 53

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሂዷል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በዲፕሎማሲ ዘርፎች ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች በመከናወናቸው አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ሀገራዊ ምክክር የሚፈጥረውን መደላድል በመጠቀም ከሪፎርም ወደ ተሟላ የፖለቲካ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን ትግበራን ለማሳካት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ጽንፈኝነትን በመታገልና የትስስር ትርክት እንዲጎለበት ለማድረግ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር የተጀመሩ የስታንዳርዳይዜሽን ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግሥት ጠንካራ መንግሥት እና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ውጤታማ የፓርቲ ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን አብራርተዋል፡፡

አመራሩንና አባሉን ጨምሮ ሁሉንም መዋቅር በማነቃነቅ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋልም ነው ያሉት፡፡

በየደረጃው ያለው አመራርና አባል የተሰጠውን ኃላፊነት በጥራትና በውጤታማነት መፈጸም እንደሚገባ የገለጹት አቶ አደም፣ የጽሕፈት ቤቱ አመራርና ሠራተኛም በበጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ማቅረባቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: