Search

የስፔን ላሊጋ ዛሬ ይጀመራል

ዓርብ ነሐሴ 09, 2017 465

የ2025/26 የስፔን ላሊጋ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡ ጂሮና ከራዮ ቫይካኖ ምሽት 2 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 16ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ጂሮና በሜዳው የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ተሳታፊ ከሆነው ራዮ ቫይካኖ ይጫወታል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ደግሞ ቪያሪያል ከ ሪያል ኦቪዲዮ ይጫወታል፡፡ ከ24 ዓመታት በኋላ ወደ ላሊጋው የተመለሰው ሪያል ኦቪዲዮ ከሜዳው ውጭ ከቪያሪያል በሚያደርገው ጨዋታ ሊጉን የሚጀምርም ይሆናል፡፡
በዝውውሩ ቶማስ ፓርቴን ያስፈረመው ቪያሪያል አጀማመሩን ለማሳመር ወደ ሜዳ በሚገባበት ጨዋታ ከሊጉ እንግዳ ቡድን ከባድ ፈተናም ይጠብቃዋል፡፡
የቀድሞው የአርሰናል አማካይ ሳንቲ ካዞርላ ከልጅነት ክለቡ ጋር የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ